ስልት
አንቀጽ 3፡ የማህበሩ ስልት
3.1 በኒውዮርክና አከባቢዉ አካባቢው የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በአንድ ላይ ተሰባስበው አገር ቤት እየተካሄደ ያለውን የአማራን የዘር ፍጅት ለማስቆም የሚታገሉ ወገኖቻችን መርዳት
3.2 የአማራን ባህል ልምድና ቋንቋ መጠበቅና፤ ማበልጸግና ማዳብር
3.3 በአማራ ህዝብ ላይ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ሲከሰት ለችግሩ መድረስ፤
3.4 የሌላውን ብሔረሰብ ባህል፣ ቋንቋ፣ የግዛት አንድነትና የሰባዊ መብት ያከብራል።
3.5 የአማራ ሕዝብንና የዚህ ማህበር አባላትን የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብት ንቃት ደረጃቸውን ከፍ ማድረግ
3.6 በታሪካቸው የአማራ ግዛት የነበሩትን አሁን ግን በጉልበት በሌላ የተነጠቁትን መሬቶች ለማስመለስ በሚደረገው ትግል ያግዛል ይተባበራል።
3.7 የአማራ ሕዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር በሚደረገው ትግል ሙሉ ተሳትፎ ያደርጋል።
3.8 የአማራ ህዝብ ፍትሀ እንዲረጋገጥለትና በሰላም የመኖር መብቱ እንዲከበርለት አጥብቆ ይታገላል።
3.9 የአማራን ሕዝብ መብቶች በሚጥስ ግለሰብ፤መንግስትም ሆነ ድርጅት ላይ ያላለሳለሰ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግና እንዲሁም የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አባላትንና ሴኔተሮችን በማነጋገር ችግሩን ማስረዳትና ለሕዝባችን የሚጠቅም ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ግፊት ማድረግ።
3.10 የኢንተርኔት፣ የሚድያንና የቴሌቪዥን ስርጭት በመጠቀም የኢትዮጵያንና ለተቀሩት የዓለም ሕዝቦች ስለ እውነተኛ የአማራን አጀንዳ እንዲገነዘቡ ማድረግ።